id stringlengths 9 150 | url stringlengths 42 183 | title stringlengths 11 101 | summary stringlengths 45 356 | text stringlengths 439 6.59k |
|---|---|---|---|---|
a_g20-toronto-canada-meeting-06-28-10-97331599_1460839 | https://amharic.voanews.com/a/g20-toronto-canada-meeting-06-28-10-97331599/1460839.html | የG20 አገሮች መሪዎች በቶሮንቶ ካናዳ ተሰባሰቡ | በሶስት ዓመታት ውስጥ የባጀት ኪሳራቸዉን በግማሽ እንዲቀንሱ ፣ እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር እስከ 2016 ደግሞ ከኢኮኖሚ እድገታቸዉ ጋር በማጣመር ተጨማሪ የባጄት ኪሳራ ቅነሳ ማድረግ አለባቸዉ አሉ። | የዓመት የባጄት ኪሳራቸውን እየቀነሱ የኢኮኖሚ እቅዳቸውን ከግብ የማድረስ ግዴታ እንዳለባቸው መክረዋል ስምንት በኢኮኖሚ ከበርቴ የሆኑ እና ኢኮኖሚያቸዉ እየመጠቀ ያለ እንደ ቻይናና ህንድ ያሉ ታዳጊ አገሮችን የጠቀለለ የ G 20 መሪዎች ጉባኤ በቋፍ ያለ የዓለም ኢኮኖሚ አሁንም ማነቃቂያ እንደሚያሰፈልገውና የበጀት ኪሳራቸውን ለመቀነሰ ግን የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ እንዳለባቸው ተስማምተዋል። ጉባኤዉን ባስተናገደችው አገር ካናዳ ባቀረበችው እቅድ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ስቲቨን ሀርፐር የኢኮኖሚ ተሃድሶው እንዲቀ... |
a_amnesty-open-letter-to-the-ethiopian-parilament-voa-03-01-18_4276606 | https://amharic.voanews.com/a/amnesty-open-letter-to-the-ethiopian-parilament-voa-03-01-18/4276606.html | አምነስቲ ለኢትዮጵያ ፓርላማ ግልጽ ደብዳቤ ጻፈ። | “አሳሳቢውን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተልን ነው። አሁን ላለው ችግር መብትን ይበልጥ መገደብ አይደለም መልሱ።” ሳሊ ሼቲ የአምነስቲ የሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር። | ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ለኢትዮጵያ ፓርላማ አባላት ግልጽ ደብዳቤ ልኳል። የምክር ቤቱ አባላት ነገ አርብ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ለመምከር እየተዘጋጁ ባሉበት በዚህ ወቅት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ይበልጥ እንዲያስቡ ጥሪ እናቀርባለን፤ ብሏል። በነገው የፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዙሪያ ክርክር የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አብይ ትኩረት እንዲሆን ነው፤ አምነስቲ በግልጽ ደብዳቤው የጠየቀው። የኢትዮጵያ ፓርላማ አዲሱ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀድሞውንም የጠበበው... |
a_india-covid19-surpases-20-million-second-wave-continues-05-04-21_5878097 | https://amharic.voanews.com/a/india-covid19-surpases-20-million-second-wave-continues-05-04-21/5878097.html | መቆሚያ ያልተበጀለት የህንዱ ሁለተኛ ዙር የኮቪድ 19 ማዕበል | “አጋዥ ከማጣት የመጣ አይደለም። ጨርሶ ከመውደቅ ደረጃ መድረሱ እንጂ! ለሌላ ለማዘን ከምንችልበት ቦታ አይደለንም። እዚህ ታካሚዎች እየሞቱብን ነው። ይሄ የተለየ ድብቅ ምክኒያት የከሰተውም አይደለም።በተጨባጭ የሚታይ ነገር ነው። ሁሉም ያውቀዋል፡፡ አገረ ገዥው ያውቁታል። አስተዳደሩም ያውቀዋል። ሁሉም ያውቀዋል፡፡” ዶ/ር ሩሺ ጉብታ በማዕከላዊ ኒው ዴልሂ የሚገኝ ሆስፒታል የጽኑ ህሙማን ሃኪም። | ዋሺንግተን ዲሲ — ህንድን እያናወጠው ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዛሬ 13ተኛ ቀን በተከታታይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ለቫይረሱ መጋለጡ ተዘግቧል። በአንድ ቀን ዕድሜ 357 ሺህ 229 አዲስ ለኮረናቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች መዘገባቸውን የጤና ሚንስትር በዛሬው ዕለት አስታውቋል። ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በደቡባዊ እስያዊቱ አገር በኮቪድ-19 ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉት ከ3449 በላይ ሰዎች ናቸው። በጃን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የኮረናቫይረስ መረጃ ማዕከል አሃዞች መሰረት ባሁኑ ወቅት በህንድ ለቫይረሱ ... |
a_opposition-wants-new-election-06-03-10-95522759_1458002 | https://amharic.voanews.com/a/opposition-wants-new-election-06-03-10-95522759/1458002.html | የኢትዮጵያው ምርጫና የተቃዋሚዎቹ የዛሬ አቋም | የመንግሥት ባለሥልጣናት የገዥው ፓርቲ አጠቃላይ ድል የሕዝቡን ፍላጎት ያሣየ ነው ቢሉም ተቃዋሚዎቹ ግን ምርጫው ተሠርቋል በሚል አቋማቸው እንደፀኑ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት አዲስ ምርጫ ጠይቀዋል፡፡ | "ፍትሐዊ ምርጫ ቀልድ ነበር" - ኢፍዴኃግ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ስምምነት የሌላቸው 65 ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው ከተደረሰባቸው ሰባሪ ሽንፈት ለማገገም እየተፍጨረጨሩ እንደሆነ ይታያል፡፡ ብዙዎቹ ግን በአንድ ጉዳይ ላይ ወደአንድ ሠልፍ እየገቡ ይመስላሉ - በምርጫው ውጤት፡፡ ከ547ቱ የፓርላማ መቀመጫዎች አሥር ከመቶ የማይሞሉትን የተቃዋሚ የሚባሉ መቀመጫዎች በብዙ መንገድ ነው የሚቀራመቷቸው፡፡ የስድስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረቱ የኢትዮጵያ የፍትሕና የዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር አዲስ ምርጫ መካሄድ አለበ... |
a_amh-horn-drought-moyale-cattle-death-10-11-11-131540858_1462986 | https://amharic.voanews.com/a/amh-horn-drought-moyale-cattle-death-10-11-11-131540858/1462986.html | በደቡብ ኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በተጨማሪ የዝናብ እጥረት ተባብሷል | በቦረና ዞን ክፉኛ በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች የመስከረም አጋማሹ ዝናብ ዘግይቷል | ከአዲስ አበባ 705 ኪሜ ወደ ኢትዮጵያ ኬንያ ድንበር ሞያሌ መንገድ ጸሃይ በርትታለች። ክው ብለው በደረቁት የግራር ዛፎችና ቁጥቋጦዎች ያለከልካይ የሚነፍሰው ንፋስ ደማቅ ብርቱካናማውን አፈር እንዳሻው ይገልጠዋል። ድርቁ አካባቢውን አረንጓዴ ቀለም አይቶ የማያውቅ በረሃ አስመስሎታል። ግራና ቀኝ በቀይ አፈር አጃቢነት ከተነጠፈው አስፋልት ቀለሙ በለቀቀ ጥቁርና ነጭ ቀለም 705 ኪሎሜትር የሚል የኮንክሪት አምድ ቆሟል። ከአዲስ አበባ 705 ኪ.ሜ መሆኑን ከሚያሳየው ምልክት ስር አንዲት ደባራ ላም ወድቃለች። ከ... |
a_ethiopia-election-re-run_1458682 | https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-election-re-run/1458682.html | «በአብዛኛው ታዛቢዎቻችን በሌሉበት ተካሄደ፤» ሲሉ፥ የገለፁት የግንቦት 15ቱ ምርጫ እንዲደገም ሁለት ዋነኛ ተቃዋሚ ቡድኖች አስታወቁ። | «ነፃና ገለልተኛ የሆኑ የአገር ውስጥና የውጭ አገርና ታዛቢዎች፤ በተገኙበት ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ እንጠይቃለን፤» - መድረክ | «የምርጫው ሂደትም ሆነ የድምፅ መስጫው ቀን፥ ነፃና ፍትሃዊ ባለመሆናቸው፤ ታዛቢዎቻችን ተደብድበው በመባረራቸው በብሄራዊው የምርጫ ቦርድ ይፋ የተደረገውን ውጤት አንቀበልም። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ዛሬ በተከታታይ በሰጧቸው መግለጫዎች በምርጫ ቦርድ ይፋ የተደረገውን ውጤት እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል። ምርጫ ቦርድ ውጤቱን ይፋ ካደረገና ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግም ድሉን ማክበር ከጀመረ በኋላ የመጀመሪያው በሆነው ይፋ የተቃዋሚዎች መግለጫ ሁለቱ ተቃ... |
a_voa-amharic-news-05-22-2020_5442495 | https://amharic.voanews.com/a/voa-amharic-news-05-22-2020/5442495.html | ቪኦኤ አማርኛ - የቅዳሜ፤ ግንቦት 22/2012 ዜና | በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ተጋላጭ ከአንድ ሺህ በላይ ሆነ ከቤይሩት ተጨማሪ 323 ሃገራቸው ገቡ የጆርጅ ፍሎይድ መገደል ዓለም አቀፍ ንግግር እየሆነ ነው | ኢትዮጵያ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ መጋለጣቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ ስድሣ መብለጡን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የኮቪድ 19 ሞት ቁጥር ስምንት መድረሱን በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፊርማ የወጣው የዛሬ መግለጫ ያሳያል። መግለጫው ዛሬ እስከወጣበት ጊዜ በነበሩት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረጉ 5 ሺህ 34 የላብራቶሪ ምርመራዎች ለቫይረሱ መጋለጣቸው የተረጋገጠው ዘጠና አምስት ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች አጠቃላይ ቁጥር ዛሬ 1063 ደርሷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኮቪድ 19 የ... |
a_article----112273904_1460523 | https://amharic.voanews.com/a/article----112273904/1460523.html | ሁለት ጥበበኛ እጆች | አብዱረዛቅ ረሽድ ወይንም በመድርክ ስሙ አብዲ ዘ-ጀግለር ታዋቂ የሰርከስ ትርዒት ባለሙያ ነው። ስለትግሉና ስኬቱ ከመስታዎት ዝግጅት ጋር ተወያይቷል። | ተወልዶ ያደገው ናዝሬት ከተማ ነው። አብዱረዛቅ ረሽድ አደም ገና በስምንት ዓመቱ የሰርከስ ልምምድ ለማድረግ ከትምህርት ቤት መልስ ከበጎ ፈቃድ አሰልጣኙ ሙያ ሊቀስም ሲሄድ ቤተሰቦቹ ደስተኞች አልነበሩም። “ይሄንን ቧልትና ዝላይ ትተህ በትምህርትህ በርታ” ነበር የወላጆቹ ምክር። በየቀኑ ወሳኝ ክህሎቶቹን እየተማረ የነበረው አብዲ ግን ተደብቆም ቢሆን ከልምምድ አይቀርም ነበር። “ቤተሰቦቼ ጊዜየን የከንቱ የማሳልፍ ይመስላቸው ነበር” ይላል አብዲ። የኋላ ኋላ ቤተሰቦቹን ከትርዒቶቹ አንዱን እንዲመለከቱለት ጋብዟ... |
a_amh-ethiopians-eritreans-libya-02-25-11-116949553_1458016 | https://amharic.voanews.com/a/amh-ethiopians-eritreans-libya-02-25-11-116949553/1458016.html | ሁለት ኢትዮጵያዊያን በሊቢያ መሞታቸውንና በርካታዎች መሰወራቸውን ስደተኞቹ አስታወቁ | በጸረ-መንግስት ተቃውሞ በታወከችው ሊቢያ አፍሪካዊያን ስደተኞች ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰባቸው ይገኛል። በተለይ ከመንግስቱ ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ከተሞች ጥቃቱ አይሏል። | የጋዳፊ ቅጥረኞች ናችሁ በሚል ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ጥቃት እየደረሰባቸው ነው በጸረ-መንግስት ተቃውሞዎች የተናወጠችውን ሊቢያ ለቀው ለመውጣት በርካታ ሽህ የውጭ አገር ስደተኞች በአውሮፕላን፤ በመርከብና በእግር እየተመሙ ባለበት ወቅት ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን በከባድ ችግር ውስጥ ወድቀዋል። በዚህ ግጭት መሀል የተያዙት በሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ስደተኞች የሞማር ጋዳፊ ቅጥረኛ “ጥቁር የውጭ አገር ወታደሮችሁ” ናቸው በሚል ለድብደባ፣ ዘረፋና ግድያ መጋለጣቸውን ይናገራሉ። በጸረ-መ... |
a_ethiojazz-music-young-ethiopia-_3187096 | https://amharic.voanews.com/a/ethiojazz-music-young-ethiopia-/3187096.html | አዳጊ ወጣት የጃዝ ሙዚቃ ተጫዋቾች-በካሊፎርኒያ | “Young Ethio-jazz Band” በሚል ስያሜ ይታወቃሉ። ተወልደው ያደጉት በዩናይትድ ስቴትስ ኦክላንድ ካሊፎርኒያ ነው። እድሜያቸው ከዐስራ ሦስት እስከ ዐስራ ስምንት የሆኑት አነዚህ ወጣቶች በጋራ ሙዚቃን መጫወት የጀመሩት የዛሬ አራት ዓመት ነው።"ኢትዮጵያዊነታችሁን ለማስተዋወቅ አትፈሩ" ይላል ከሙዚቃ ባንድ አባላት አንዱ። | ዋሽንግተን ዲሲ — ኢትዮጵያዊ ዜማዎችን በተለያዩ መድረኮች በመጫወት ለውጭው አድማጭ ኢትዮጵያዊነታቸውና ባህላቸውን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ። በተለይም የኢትዮ-ጃዝ የሙዚቃ ስልት የሆነውን የዶ/ር ሙላቱ አስታጥቄ ሙዚቃዎችን በመድረክ በመጫወት ይታወቃሉ። 'Young Etho-jazz band' ያንግ ኢትዮ-ጃዝ ባንድ የተመሰረተው በአዳጊዎቹ ወላጆች የጠነከረ ጓደኝነትና ኢትዮጵያዊነትን ለልጆቻቸው ለማስተላለፍ ካላቸው ፍላጎት ነበር። ከሙዚቃ ባንድ አባላቱ የአንዱ ልጅ አባት የሆነው አቶ ሲራክ ተግባሩ በተለየ የኢ... |
a_amh-unsc-eritrea-react-12-6-11-135127608_1458866 | https://amharic.voanews.com/a/amh-unsc-eritrea-react-12-6-11-135127608/1458866.html | ኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ተጨማሪ ማእቀብ የጣለብኝ ለዩናይትድ ስቴይትስ ስለማላጎበድድ ነው አለች | ኤርትራ በምስራቅ አፍሪካ የምትፈጥረውን አለመረጋጋት ለመግታት በሚል ያለፈው ውሳኔ 2023 በኤርትራ የማእድን ኢንዱስትሪና በውጭ አገር የሚኖሩ ኤርትራዊያን የሚከፍሉት ቀረጥ ለአፍራሽ ተግባር እንዳይውል ያቅባል። | ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቪዛ ማግኘታቸውን ዩናይትድ ስቴይትስ ገለጸች በኤርትራ ላይ ተጨማሪ ማእቀብ ከመጣሉ በፊት የምስራቅ አፍሪካ አገሮች ህብረት IGAD መሪዎችና ተወካዮቻቸው በአዲስ አበባ በቪዲዮ መልእክት የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ማእቀብ እንዲጥል ጠይቀዋል። የጸጥታው ምክር ቤት አባላት አንዲያስቡበትና ድምጻቸውን እንዲሰጡበት የረፍት ጊዜ ከወሰደ በኋላ በናይጀሪያና ጋቦን አርቃቂነት የቀረበው ስምምነት 2023 በ13 የድጋፍ ድምጽና በቻይናና ራሻ ተአቅቦ ጸድቋል። በተ... |
a_eritrean-sanctions-united-nations-07-21-10-98943239_1460405 | https://amharic.voanews.com/a/eritrean-sanctions-united-nations-07-21-10-98943239/1460405.html | የኤርትራ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጣለባትን ማእቀብ እንዲያነሳ ጠየቀች | ኤርትራ ይህንን ጥያቄዋን ያቀረበችው ከጅቡቲ ጋር ያላትን የድንበር ግጭት በውይይት ለመፍታት የጀመረችውን ጥረት ካወደሰ በኋላ ነው። | አንድ የዩናይትድ ስቴይትስ የረጅም ጊዜ የህግ አውጭ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርትራን አሸባሪዎችን ከሚረዱ አገሮች ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንድትገባ ጠይቀዋል ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ባን-ኪሙን ቢሮ የወጣው ሪፖርት ኤርትራ ከጎረቤቶቿና ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ገንቢ በሆነ መልኩ እየተነጋገረች መሆኑን ጠቁሟል። በተለይ ኤርትራ ከጅቡቲ ጋር ያላትን የድንበር ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት መወሰኗ ይበል የሚያሰኝ ጅምር መሆኑን አትቷል። የጸጥታው ምክር ቤት በኒው ዮርክ ሲሰበሰብ በጉዳዩ ላ... |
a_rockwell-exhibit-contest10-13-10-104895464_1460770 | https://amharic.voanews.com/a/rockwell-exhibit-contest10-13-10-104895464/1460770.html | የአሜሪካዊያን ኑሮ በየኖርማን ሮክዌል ስእሎች | በእርሳስና በዘይት በሚስላቸው እውነት መሰል ስእሎች በዋሽንግተን ዲሲ በመታየት ላይ ናቸው። በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኢምባሲ የጥበብ ውድድር ከፍቷል። | በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናትድ ስቴይትስ ኢምባሲ በሚቀጥለው አመት የሚከበረውን የፕሬዝደንት ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዝቬልት “የአራቱ ነጻነቶች” ንግግር አስመልክቶ የጥበብ ውድድር አዘጋጅቷል። የፕሬዝደንቱ ንግግር የመሰጠው አሜሪካዊ ሰአሊ ኖርማን ሮክዌል በ1935 ዓ.ም “የአሜሪካ ኑሮ” በሚል አራት የስእል ራብአይ ለትእይንት አብቅቷል። እነዚህ ታዋቂ ስእሎች በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ እየታዩ ይገኛሉ። በዋሽንግተን ዲሲ እምብርት የሚገኘው የስሚትሶኒያን ማእከል የታዋቂውን አሜሪካዊ ሰአሊ ኖርማን ሮክዌል ስራዎች ... |
a_amh-ak-us-midterm-elections-global-implications-analysis-106476383_1458441 | https://amharic.voanews.com/a/amh-ak-us-midterm-elections-global-implications-analysis-106476383/1458441.html | የዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤቶች ምርጫና ዓለም አቀፍ አንድምታው | ሪፐብሊካኖች ምርጫውን አሸንፈው ሁለቱንም ምክር ቤቶች ወይም አንዱን ብቻ እንኳን ከቆጣጠሩ፥ የፕሬዝዳንት ኦባማ አስተዳደር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከተላቸውን ፖሊሲዎች አስመልክቶ በርከት ያሉ ለውጦች ሊመጡ ይችላሉ። | በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ማክሰኞ ጥቅምት 23 የሚካሄዱት Midterm Elections በመባል የሚታወቁት የአጋማሽ ጊዜ ምርጫዎች፤ በአሁኑ ወቅት አብላጫውን የሁለቱን ምክር ቤቶች የኅግ አውጪውንና የእንደራሴዎች ምክር ቤቶች፤ መቀመጫዎች ለያዘው የፕሬዝዳንት ኦባማ የዲሞክራቶች ፓርቲ ፈተና ይደቅናል፤ ተብሎ ተገምቷል። የሪፐብሊካኑ ፓርቲ የብልጫውን ድምፅ ያገኝ ይሆናል፤ የሚል ሠፊ ግምት በተያዘባቸው በእነኚህ የአጋማሽ ጊዜ ምርጫዎች፤ በርካታ መቀመጫዎችን ያጡ ይሆናል የተባሉት ዲሞክራቶች፥ ከተቀናቃኛቸው በሚገ... |
a_osaman-mohammed092910-104029894_1460868 | https://amharic.voanews.com/a/osaman-mohammed092910-104029894/1460868.html | የኤርትራ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን መሀመድ ሳለህ የኤርትራ መሬት በኢትዮጵያ በህገ ወጥ ሲያዝ ባለማስለቀቅ የመንግስታቱን ድርጅት ወነጀሉ | ዉዝግቡ የሚመለከታቸዉ አካላት ሃላፊነት ካልሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማደራደር ስልጣን የለዉም ብለዋል አቶ ስዩም መስፍን ። | አቶ ኦስማን የግጭት መቀጠል ለኤርትራና ኢትዮጵያ ህዝቦች ከባድ ሸክም ከመሆኑም በላይ የአካባቢዉን ሁኔታ የሚያወሳስብ ነዉ ሲሉ,የኢትዮጵያዉ አቻቸዉ አቶ ስዩም መስፍን በበኩላቸዉ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንበሩን ለማካለል ያቀረበዉ ዉሳኔ ላይ ”አልወያይም” ያለችዉ ኤርትራ ናት ብለዋል። የኤርትራ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን መሀመድ ሳለህ የኤርትራ መሬት በህገ ወጥ በኢትዮጵያ ሲያዝ፣ አይቶ እንዳላዬ ቸል በማለት የመንግስታቱን ድርጅት ከሰዋል። ኢትዮጵያ የኤርትራን ነጻ ግዛት እንደያዘች ሲሆን፣ የተባ... |
a_amhara-landslide-08-24-10-101405284_1461942 | https://amharic.voanews.com/a/amhara-landslide-08-24-10-101405284/1461942.html | በአማራ ክልል የመሬት መንሸራተት 19 ሰዎችን ገደለ | በመርሳ ከተማ በደረሰው የመሬት መንሸራተት 14 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ 24 ቆስለዋል። በውርጌሳ ዙሪያ አምስት ሰዎች ሞተዋል። | አከታትሎ የጣለ ዝናብ ያደረሰው የጎርፍ አደጋ በሀብሩ 2ሽህ ሰዎችን አፈናቅሏል አቶ አሰፋ ነጋሲ በሀብሩ ወረዳ በመርሳ ከተማ ለረጂም ጊዜ የኖሩ የአገር ሽማግሌ ናቸው። አበይ ተራራ በሚባለው ስፍራ ከሰሩት ቤታቸው ቁልቁል ከተማዋን እየተመለከቱ የህዝቡ ብዛት ከጥቂት ሽዎች ወደ አስር ሽዎች ሲያድግ ተመልከተዋል። በግብርና ስራ የተሰማሩት አቶ አሰፋ ቤት እሁድ ሌሊት በመሬት መንሸራተት ፈርሷል። አቶ አሰፋ ምሽቱን አነስ ባለች ቤት ስላሳለፉ በአደጋው ጉዳት አልደረሰባቸውም። በዋናው ቤት ውስጥ የነበሩት ባለቤታ... |
a_ethiopia-press-review-8-23-13_1735792 | https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-press-review-8-23-13/1735792.html | ኢትዮጵያ በጋዜጦች | የሱዳንና የሶማልያ ፕረዚዳንቶችን የመሳሰሉት በዝክረ መለስ ስነ-ስርአት የተሳተፉት የአፍሪቃ መሪዎች “የአፍሪቃ ድምጽ” በማለት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትርን አሞግሰዋል። | ዋሽንግተን ዲሲ — ዋሽንግትተ ፖስት ጋዜጣ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትርመለስ ዜናዊ ህልፈት አንደኛ አመትን ለማሰብ ስለተደረገው ስነስርአት ባወጣው የአሶሼተድ ፕረስ ዘገባ አቶ መለስ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ አንድ አመት ቢያልፍም የተለወጠ ነገ የለም ይላል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አመቱን ሙሉ ሲሞገሱ ቆይተዋል። ምስላቸውም በሀገሪቱ ዙርያ በሚገኙት የመንግስት መስርያ ቤቶች እንደተሰቀለ ነው ይላል ጋዜጣው ላይ የወጣው ዘገባ። በሀገሪቱ ዙርያ የሻማ ማብራት ስነ-ስርአት ተደርጎላቸዋል። ለሳቸው ማስታውሻም ከአርባ ... |
a_the-idea-series-ethiopian-history-selective-memory-a-historian-view-voa-dr-shimelis-bonsa-with-alula-kebede-july-2017_3968766 | https://amharic.voanews.com/a/the-idea-series-ethiopian-history-selective-memory-a-historian-view-voa-dr-shimelis-bonsa-with-alula-kebede-july-2017/3968766.html | ታሪክ ‘ባስታዋሹ’ መነጽር እና ...በታሪክ ምርምርና ፋይዳ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሌሎች ወጎች | “ክርክሩ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን መነጋገሪያ መድረክ የት ነው? እያንዳንዱ ሰው ከራሱ መንገድ ነው የሚጽፈው። በታሪክ ሞያ ውስጥ ይሄን ምንድን ነው የምንለው? መርጦ ማስታወስ እና መርጦ መርሳት። የተወሰኑ ነገሮች ተመርጠው ይታወሳሉ። ተመርጠውም ይረሳሉ። ታዲያ እነኚህ ጨርሶ እውነታ የላቸውም ማለት አይደለም። ነገር ግን ጎዶሎ እውነታዎች ነው የሚሆኑት። የራስን ፍላጎት ለማስፈጸም ነው የሚውሉት።” ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ። | አዎን! ይህም “ሃሳብ እንደ መንገድ .. በማስረጃ የተደገፉ ጠቃሚ ወጎች” በሚል አብይ ርዕስ የተጀመረው አዲስ ተከታታይ ወግ አካል ነው። የታሪክ ትንተና በፈቃድና ከጥቅም አንጻር ሲተረጎም? ... ታሪክ ባስታዋሹ መነጽር ነገር ግን በብዙዎች ህይወት ላይ የሚኖረው አንድምታ እንደምን ይታያል? የታሪክ ምርምር ተጨባጭ ፋይዳስ በእርግጥ ምንድን ነው? እንግዳችን ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ ናቸው። በState University of New York - Stony Brook የአፍሪካ ዘመናዊ ታሪክና ፖለቲካ እንዲሁም የከተማ ... |
a_article-------------114307439_1460381 | https://amharic.voanews.com/a/article-------------114307439/1460381.html | ቻይና ከዩናይትድ ስቴይትስ ጋር የጠበቀ የንግድ ግንኙነት እንጂኖራት ፕሬዝደንት ሁ ጥሪ አቀረቡ | ዩናይትድ ስቴይትስን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የቻይናው ፕሬዝደንት ሁ ጂንታው አገራቸው ከአሜሪካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖራት እንደምትፈልግ ገልጸው፤ ቻይና አጋር እንጂ ስጋት አይደለችም ብለዋል። | የቻይናው ፕሬዝደንት ሁ ጂንታው በዩናይትድ ስቴይትስ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። ከ1989ወዲህ በዩናይትድ ስቴይትስ መንግስታዊ ልዑካንን በመምራት የቻይና ፕሬዝደንት ወደ ዩናይትድ ስቴይትስ ሲጓዝ ሁ የመጀመሪያው ናቸው። በዚህ ጉብኝታቸው ሚስተር ሁ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በአንድሩውስ ወታደራዊ የአውሮፕላን ማረፊያ በምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ዛሬ በዋይት ሀውስ ቤተ-መንግስት ከፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። የአሜሪካ ኩባንያዎችና ድርጅ... |
a_the-purpose-of-education-experts-discuss-the-state-of-education-in-ethiopia-with-voa-alula-kebede-march-1-2021_5799589 | https://amharic.voanews.com/a/the-purpose-of-education-experts-discuss-the-state-of-education-in-ethiopia-with-voa-alula-kebede-march-1-2021/5799589.html | ለምን እንማራለን? | "..ራሳችን በራሳችን የመሠረትነው ትምህርት ከኖረን ቆይቷል።.." ዶ/ር ሃዋኒ ንጉሴ "የራሳቸው ነጻነት ኖሯቸው ማሰብ መፈተሽ እንዲችሉ - ተዓማኒነት ያለውን ከሌለው መለየት የሚያስችል የአስተሳሰብ ችሎታ፥ የሰው መብት የሚያከብር ፍጡር እንዲሆኑ ለማድረግ የምንጠቀምበት ሂደት ነው።" ዶ/ር አዳነ ገበያው ካሳ። "..ከዛሬ የተሻለ ነገ እንዲኖረን የሚረዳ እና ችግርን የሚፈታ መሆን አለበት ብዬ ነው የማምነው።.." ዶ/ር ፋንታሁን አድማስ። | ዋሽንግተን ዲሲ - ሎሳንጀለስ - ሺካጎ - አዲስ አበባ — በዝግታ … በጊዜ ውስጥ በሚገበይ እውቀት ሁነኛ ለውጥ ማምጣት ቻሉና “ለአንዳች ቁም ነገር ማብቃቱ” የታወቀና ሁሌም የሚጠበቅ ትሩፋቱ ይመስላል። ኑሮን ለማሸነፍ የሚበጅ ክህሎት ማጎናጸፉና የሰው ልጆችን ህይወት ለማሻሻል ዓይነተኛ መንገድነቱ ሳይሆን ዕድሉን ማግኘት ያለማግኘት ነው ጥያቄው። የመልካም ፍሬዎቹን መበርከት: የመንገዱን ማለቂያ ያለው ያለመምሰል እና ጉዞው የዕድሜ ልክ የሆነውን ያህል ግን አንዳንዶች በዙሪያቸው ያለውን ዓለም አይተው መለስ... |
a_amh-ned-havel-1-11-2012-137122993_1460387 | https://amharic.voanews.com/a/amh-ned-havel-1-11-2012-137122993/1460387.html | በኢትዮጵያ መንግስት የሚዋከቡና የሚታሰሩ ተጠቂዎች ቢመስሉም አሸናፊዎች ናቸው ሲሉ ብርቱካን ሚደቅሳ ተናገሩ | በዋሽንግተን ዲሲ በተሰናዳ የቀድሞው የቼኮዝላቫኪያ ፕሬዝደንት ቫትስላቭ ሃቨል መታሰቢያ የብርማዋ አንሳንሱቺ፣ ፕሬዝደንት ኦባማ፣ ዳሊ ላማና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች መልእክት አስተላልፈዋል | በታህሳስ ወር በህመም የሞቱት የቀድሞው የቼኮዝላቫኪያ ፕሬዝደንት ቫትስላብ ሃቨል፤ ቼኮስላቫኪያን ከኮሚውኒስት አገዛዝ ነጻ ለማውጣት “የቬልቬት አብዮት” በመባል በሚታወቀው ሰላማዊ ትግል በ1981ዓም የቼኮዝላቫኪያ ፕሬዝደንት ሆኑ። በ1985 ቼኮዝላቫኪያ ለሁለት ተከፍላ ስሎቫኪያና ቼክ ሪፐብሊክ ስትባል፤ የመጀመሪያው የቼክ ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል። ቫትስላቭ ሃቨል በመላው አለም የሚታወቁት በፖለቲካቸው ብቻ አይደለም። እንዲያውም ሃቨል ከምንም በላይ እራሳቸውን የሚገልጹት፤ ጸሃፊ ተውኔት አድርገው ነው።... |
a_ethiopia-health-11-12-10-109949584_1458542 | https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-health-11-12-10-109949584/1458542.html | የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ ለማሳደግ ዩናይትድ ስቴይትስ ተጨማሪ እገዛ እያደረገች ነው | ኢትዮጵያ በዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት የግሎባል ሄልዝ ኢኒሺየቲቭ በጤና ዙሪያ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣሉ ተብለው ከተመረጡ ጥቂት አገሮች አንዷ ነች። | በአማራ ክልል የኦሮሚያ ዞን በሚገኘው የባቲ የጤና ጣቢያ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኛ የሆነችው ዘቢባ ሰይድ መድሃኒቶችን ከመድሃኒት ቤት ለመውሰድ መጥታለች። መድሃኒት ቤቱ ተጨናንቋል። ከኦሮሚያ ዞንና ከቅርበቱ አንጻር ከአፋር ክልል የሚመጡ ተገልጋዮች በጤና ጣቢያው ይገኛሉ። ይሄንን መሰል የጤና ጣቢያ በተለይ በገጠር አካባቢ ማግኘት አይቻልም። ለዚህ ነው የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ምንስቴር የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ያሰማራው። እንደ ዘቢባ መሰል ከ32ሽህ በላይ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞ... |
a_unga-obama-ahmadinejad--103885994_1461881 | https://amharic.voanews.com/a/unga-obama-ahmadinejad--103885994/1461881.html | "ታሪክ የነፃነት ወገን ነች" - ፕሬዚዳንት ኦባማ ለተመድ ያደረጉት ንግግር | "በመስከረም 94ቱ ጥቃት ውስጥ የአሜሪካ መንግሥት እጅ አለበት" - ፕሬዚዳንት አሕመዲነጃጅ ለተመድ ያደረጉት ንግግር | ኒው ዮርክ ላይ ሲካሄድ በሰነበተውና 14ዐ የሚሆኑ የመንግሥታትና የሃገሮች መሪዎች በተገኙበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ የሐሙስ ውሎ ላይ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ፕሬዚዳንቶች ተናግረዋል፡፡ ኒው ዮርክ ላይ ሲካሄድ በሰነበተውና 14ዐ የሚሆኑ የመንግሥታትና የሃገሮች መሪዎች በተገኙበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ የሐሙስ ውሎ ላይ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ፕሬዚዳንቶች ተናግረዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የሃገራቸውን ሠላም፣ የውጭ ፖሊሲና ሰብዓዊ ... |
a_article----------amh-ak-crossfire-freedom-of-speech-2-18march2011-118338139_1458396 | https://amharic.voanews.com/a/article----------amh-ak-crossfire-freedom-of-speech-2-18march2011-118338139/1458396.html | የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፥ የዛሬ ይዞታውና አካሄዱ፤ ከየት ወደ የት? | «እኔ ባለኝ ግንዛቤ፥ የንግግር ነፃነት ዛሬ በኢትዮጵያ አለ፤» አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ። «የንግግር ነፃነት ለተወሰኑ ብቻ የተሰጠ የኢህአዴግን ዓላማ ለማስፈፀም ብቻ የዋለ እንጂ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ የለም፤» አቶ ግዛው | «የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፤ ወቅታዊ ይዞታና አንድምታው፤» በእሰጥ አገባ የተጀመረው የሁለት ወገን ክርክር ቀጥሏል። የክርክሩ ተሳታፊዎች፥ አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ ከአዲስ አበባ፤ አቶ ግዛው ለገሰ ደግሞ ከዚህ ከዋሽንግተን ዲሲ ናቸው። አቶ ተስፋዬ ”የንግር ነፃነት“ ዛሬ በኢትዮጵያ «ተረጋግጧል፤» ሲሉ፤ አቶ ግዛው በበኩላቸው፤ ከዓመታት በፊት ብልጭ ብሎ የነበረውና እንዲያድግ፥ እንዲጎለብት ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ዛሬ ጨርሶ ተዳፍኗል፤ ይላሉ። የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፥ ከማጡ ወደ ድጡ? ወይስ በእርግጥ ... |
a_obama-african-youth-leaders-white-house-08-04-10-99977454_1460122 | https://amharic.voanews.com/a/obama-african-youth-leaders-white-house-08-04-10-99977454/1460122.html | ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የአፍሪካ ሀገሮችን የወከሉ ወጣት መሪዎችን ተቀበሉ | ወጣቶቹ ከሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን እና ከአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ጆኒ ካርሰን ጋር ጀምረው ከቀትር በኋላ ደግሞ በዋይት ሃውስ ከፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ጋር በዋይት ሐውስ ምስራቅ ክፍል ውይይት አድርገዋል። | ከአሜሪካውያን አቻዎቻቸው ጋር እየተወያዩ ራዕያቸውን እያካፈሉና ልምድም እየቀሰሙ ናቸው በዚህ መልክ ነበር ፕሬኢዘንት ባራክ ኦባማ ወደ መቶ ሃያ የሚደርሱት እና በየሀገሮቻቸው የባህል ልብሶች ደምቀው በማራሹ ዙሪያ ተቀምጠው የጠበቋቸውን ወንዶችና ሴቶች የአህጉረ አፍሪካ ወጣት መሪዎች የተቀበሏቸው። ፕሬዚደንት ኦባማ ለዚህ መወያያ መድረክ ወጣቶቹን የጋበዟችው ይህ የአውሮፓውያን ሁለት ሺህ አስር ዓመተ ምህረት አስራ ሰባት የአፍሪካ ሀገሮች ከቅኝ አገዛዝ ተላቀው ነጻነታችውን የተጎናጸፉበትን ሃምሳኛ ዓመት መታሰ... |
a_th-annual-golden-globe-jan-7-2018-voa-alula-kebede_4198709 | https://amharic.voanews.com/a/th-annual-golden-globe-jan-7-2018-voa-alula-kebede/4198709.html | ኦፕራ ዊንፍሬ በዘንድሮው የምርጥ-ምርጥ የቴሌቭዥንና የሲኒማ ሥራዎች ሽልማት ጎልደን ግሎብ | “እነኚያ ሬሲ ቴይለር’ን ሊያጠፉ የሞከሩ ሰዎች በሕግ ሳይጠየቁ ቀርተዋል። ሬሲ ቴይለር ዘጠና ስምንተኛውን የልደት በዓሏን ለማክበር ጥቂት ሲቀራት ከአሥር ቀናት በፊት ነው ያረፈችው። አይደፈሬ ነገር ግን ርሕራሄ በሌላቸው ወንዶች በተደፈረ ባሕል ውስጥ አያሌ ዓመታት ኖራ አለፈች። በእነኚያ አይጠየቄ ወንዶች የደረሰባቸውን ጥቃት ለመናገር የደፈሩ ቁጥራቸው የበዛ ሴቶችም ሰሚ ሳይኖራቸው ለረዥም ዘመናት ዘለቁ። ዛሬ ግን ያ ሰዓት ያበቃ ይመስላል።” ኦፕራ ዊንፍሬ። | ዋሺንግተን ዲሲ — በቀይ ምንጣፍ ላይ የተንጣለለ የጥቁር ባሕር ተመስሏል። በሆሊውድ እና በመላዋ አገሪቱ በተለያዩ የሥራ ቦታዎች በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን ሥር የሰደደ ወሲባዊ ወከባ ለመፋለም ለሚንቀሳቀሰውን ታይም ኢዝ አፕ የተባለውን የመብት ተሟጋች ቡድን በመደገፍ ጥቁር የለበሱ በሥነ ሥርዓቱ የተገኙ ሴቶች የለበሱት ልብስ የከሰተው ገጽታ ነው። በቴሌቭዥን እና በሲኒማው መስክ ባለፈው ዓመት የተሰሩ ምርጥ ሥራዎችን የሚዘክረው የሆሊውዱ የውጭ ፕሬስ ማኅበር የሚያሰናዳውና እንደ ወትሮው ሁሉ ለየት ባለ ጉጉት ... |
a_covid-main_5545788 | https://amharic.voanews.com/a/covid-main/5545788.html | የኮሮናቫይረስ የምራቅ ምርመራ ጸደቀ | የዩናይትድ ስቴትስ የሳይንስ ምሁራን ሆስፒታል ከሚገኙት የኮቪድ 19 በሽተኞች በ 4.8 ሜትር ርቆ የቫይረሱን አካል ማግኘታቸውን ገልጸዋል። የሁለት ሜትር ርቀት መጠበቅ የሚለው እምነት የተሳሳተ መሆኑን የሳይንስ ጠቢባኑ ሲያስረዱ የነበረው የተሳሳተ ግንዛቤ ብዙ ሰዎችን ለቫይረሱ እያጋለጠ ሳይሆን አንዳልቀረ ጠቁመዋል። | ዋሽንግተን ዲሲ — ጥናቱ የተካሄደው በፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ክፍል ሲሆን ገና በሌሎች የሙያው ምሁራን እንዳልተገመገመ ተገልጿል። የአሜሪካው የል ዪኒቨርሲቲ ያፈለቀውን የኮቭድ 19 ቫረስን በምራቅ የመመርመሩ ዘዴ በአስቸኳይ ጊዜ ወቅት እጥቅም ላይ እንዲውል የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር ትላንት አጸደቀው። በምራቅ የሚደረገው ምርመራ ከ 24 ሰአታት ባነሰ ፍጥነት ውጤቱ ሊገኝ እንደሚችል ዋጋውም ርካሽ እንደሆነ ወደ $10 ዶላር ገደማ መሆኑ ተገልጿል። አዲሱ የምርመራ ዘዴ የፀደቀው ... |
a_hr-128-ethiopian-human-rights-us-congressman-cofman-01-30-18_4231874 | https://amharic.voanews.com/a/hr-128-ethiopian-human-rights-us-congressman-cofman-01-30-18/4231874.html | በUS ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ረቂቅ ሕግ ቀጣይ እጣ እና ሌሎች ቁልፍ ጉዳዮች | “ዩናይትድ ስቴትስ በክልሉ ላላት በብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ላተኮረ ግንኙነቷ ቅድሚያ በመስጠት ለረዥም ጊዜ በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጽሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አይታ እንዳላየች ስታደርግ ቆይታለች። ያ ፍጹም የተሳሳተ ነገር ነው። በመሆኑም ይሄ ያን ስህተት የማመን የመጀመሪያ እርምጃ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በገዛ ዜጎቹ ላይ የሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም።” ኮንግሬስማን ማይክል ሃዋርድ ኮፍማን የUS የተወካዮች ምክር ቤት አባል። | ዋሽንግተን ዲሲ — በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ግፊት ለማድረግ በሚል ባለፈው ዓመት በየካቲት ወር መጀመሪያ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ሕግ ቀጣይ ሂደት ዙሪያ የተካሄደ ጋዜጣዊ ጉባኤ ነው የቀጣዩ ዘገባ መነሻ። ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚታየው ሁኔታ ካልተለወጠ HR-128 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ረቂቅ ሕግ ወደ ሙሉ ምክር ቤቱ የሚተላለፍና ሊጸድቅ የሚችል መሆኑ ነው፤ በምክር ቤቱ የብዙኃኑ ፓርቲ ተጠሪ በተገኙበት በተካሄደው ጋዜጣዊ ጉባኤ የተገለጸው። በኢትዮጵያ ተፈጽመዋልና... |
a_amh-wfp-horn-drought-9-12-11-125447933_1461018 | https://amharic.voanews.com/a/amh-wfp-horn-drought-9-12-11-125447933/1461018.html | በደቡብና ምስራቅ ኢትዮጵያ ከተራቡ ሰዎች በተጨማሪ ሶማሊያዊያን ስደተኞች እርዳታ ይሻሉ | በምስራቅና በደቡብ ኢትዮጵያ የተራቡ ዜጎችና ስደተኛ ሶማሊያዊያንን ህይወት ለማዳን ከፍተኛ እርዳታ እንደሚያስፈልግ WFP አስታወቀ። ኬንያን ጨምሮ 10 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። | የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በ60 አመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ድርቅ ተመትተዋል፡፡ በዚህም መሰረት በአደጋው የተጋለጠውን ህዝብ ለመታደግ ከፍተኛ እርዳታ እንደሚያስፈልግ WFP ገልጿል። በአፍሪቃ ቀንድ በተከሰተው ድርቅ ለከፋ አደጋ የተጋለጡ ወገኖችን ለመድረስ የያዘውን ጥረት መጨመሩን የተባበሩት መንግስታት ድርግት የምግብ ፕሮግራም WFP አስታወቀ። የአሜሪካ ድምጹ ጋቢ ጆስሎ ከናይሮቢ ባጠናቀረው ዘገባ እንደጠቆመው፤ የተጎዱትን ወገኖች በአስቸኳይ ለመድረስ የሚያስፈልገውን እርዳታ ለማሟላት ድርጅቱ ለተጨማሪ... |
a_election-followup-opposition-06-08-10-95900214_1462506 | https://amharic.voanews.com/a/election-followup-opposition-06-08-10-95900214/1462506.html | ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላም ወከባና እንግልቱ ቀጥሏል፤ በሚለው ተቃዋሚና መንግስት አሁንም እየተወዛገቡ ነው | «ማንም ሰው በምንም ዓይነት ሁኔታ እንዳይዋከብ፤ የልማት ሥራው እንዳይስተጓጎል ግልፅ የመንግስት መመሪያ ወጥቷል፤» አቶ መስፍን አሰፋ። | የምርጫው ማግስት ወከባና እንግልት እንደቀጠለ ነው፤ ሲል የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬስ ገዢውን ኢህአዴግን ይወነጅላል። ኢህአዴግ በበኩሉ «ከምርጫው ጋር በተያያዘ በማንም ላይ እየተወሰደ ያለ ዕርምጃ የለም፤» ሲል ያስተባብላል። ብሄራዊው የምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መሠረት ምርጫው ሙሉ በሙሉ በኢህአዴግ አሸናፊነት ቢጠናቀቅም፤ «ለታዛቢነት ያቀረብኳቸውና ደጋፊዎቼ ከሥራ መታገድ፥ ወከባና እንግልት እየደረሰባቸው ነው፤» ሲል፥ ተቃዋሚው የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬስ ገዢውን ኢህአዴግን ወንጅሏል። ችግሮቹ ተከሰቱ የተባለበት... |
a_uganda-blast-0712-10-98264739_1462920 | https://amharic.voanews.com/a/uganda-blast-0712-10-98264739/1462920.html | በዩጋንዳ በደረሰ ፍንዳታ 74 ሰዎች ተገደሉ | በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ በደረሱ ተከታታይ ፍንዳታዎች ከ70 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ። | አስር ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን መሞታቸው ተዘግቧል ትናንት እሁድ ማታ የአለም ዋንጫ ፍጻሜን በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ በርካታ ሰዎች ተሰባስበው ሲመለከቱ ነበር ተከታታይ ፍንዳታዎች የኳስ አፍቃሪዎቹ የተሰበሰቡባቸውን ሁለት ስፍራዎች ያናወጡት። አንደኛው የዩጋንዳ ራግቢ ክበብ ሲሆን፤ ሁለተኛው በርካታ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን፣ የሌላ አገሮች ዜጎችና ዩጋንዳዊያን የተሰባሰቡበት የኢትዮጵያዊያን የገጠር ምግብ ቤት ነበር። “የመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታ በማብቃት ላይ ሳለ ነው ፍንዳታው የተከሰተው…ወዲያው ሰው ... |
a_amh-debt-us-7-20-11-125912468_1459491 | https://amharic.voanews.com/a/amh-debt-us-7-20-11-125912468/1459491.html | የዩናይትድ ስቴይትስ የብድር ጣራ በዴሞክራቶችና በሪፐብሊካኖች መካከል ያስነሳው ውዝግብ ቀጥሏል | የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት እንዲበደር የሚፈቀድለት የ14.3 ትሪሊየን ዶላር ጣራ እንዲነሳለት የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ አስተዳድር የህዝብ ተወካዮችን በኮንግረስ በመጠየቅ ላይ ነው | የዩናይትድ ስቴይትስ የብድር ጣራ መነሳትና አለመነሳት የሰሞኑ የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት ሆኖ ነው የሰነበተው። የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር በበጀት መጓደል የገጠሙትን እክሎች ሊያስተካክል፤ የመንግስቱን ወጭ በመቀነስ ላይ ባለበት ወቅት፤ አገሪቱ ተጨማሪ ብድር የምታገኝበትና፤ ከዚህ ቀደመ የቆዩ ብድሮቿን ለመክፈል እንድትችል፤ ተጨማሪ ብድር የማግኘት እድሏ በህግ ቋጠሮ ተበጅቶለታል። የባራክ ኦባማ አስተዳድር የአሜሪካ የብድር ጣራ ካልተነሳ አገሪቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ትወድቃለች በሚል አምርሮ በመከራከ... |
a_eu-election-observers-report-05-25-10-94872039_1458991 | https://amharic.voanews.com/a/eu-election-observers-report-05-25-10-94872039/1458991.html | የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን የኢትዮጵያ ምርጫ ሰላማዊ ቢሆንም በእኩል ሜዳ አለመደረጉን ገለጸ | ምርጫው ከፍተኛ ብዛት ያላቸው መራጮች የተሳተፉበትና ሰላማዊ ቢሆንም እየጠበበ በሄደው የፖለቲካ ምህዳርና እኩልነት በጎደለው የመወዳደርያ ሜዳ መዘፈቁ አልቀርም ሲሉ የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን መሪ ገለጹ። | ባለፈው እሁድ ግንቦት 15 ቀን 2002 አም በኢትዮጵያ የተካሂደውን ምክር ቤታዊ ምርጫ የተከታተለው የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን መሪ ታይስ በርማን የምርጫውን ሂደት ጠንካራና ደካማ ጎን ሲገመግሙ አራተኛው አጠቃላይ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁን ባለድርሻ አካላት በአንድነት ተቀብለውታል ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድም ምርጫውን በበቂ ሁኔታ አስተዳድሯል። ይሁንና በተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚነሱትን የኢወገኝተኛነት ጥያቄን ለመመለስ አልቻለም ብለዋል በርማን። ታይስ በርማን ይህን ያሉት ዛሬ ማክሰ... |
a_oromya-flood-08-27-10-101798503_1459111 | https://amharic.voanews.com/a/oromya-flood-08-27-10-101798503/1459111.html | በኦሮሚያ ክልል የፈንታሌ ወረዳ ነዋሪዎች በጎርፍ ተጠቃን ይላሉ፤ አስተዳደሩ ጉዳቱ መጠነኛ ነው ብሏል | በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች በተለይ በአማራ ክልል ከ37 ሰዎች በላይ የገደለው የጎርፍ አደጋ በኦሮሚያም ተከስቷል። | በኦሮሚያ በህይወት ላይ ጉዳት አልደረሰም በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ ጎርፍ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። በአካባቢው የሚገኝ የሁለተኛ ድረጃ ትምህርት ቤት ክፉኛ በጎርፍ መመታቱን ቦሩ ሮባ የተባሉ የፈንታሌ ወረዳ ነዋሪ ለቮኦኤ ገልጸዋል። “የደረሰው ጉዳት በጣም ከባድ ነው። ጉዲና ቱምሳ GTS የተባለ ሃይስኩል (ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) አለ። ያን ትምህርት ቤት እንዳለ ወስዶታል (ጎርፍ)” ብለዋል አቶ ቦሩ ሮባ። የምስራቅ ሸዋ ዞን መስተዳድር በበኩሉ መጠነኛ ጎርፍ በመተሃራ ከተማ አቅራቢ... |
a_henok-youth-white-house-08-03-10-99888544_1460928 | https://amharic.voanews.com/a/henok-youth-white-house-08-03-10-99888544/1460928.html | ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ከወጣት የአፍሪካ ሃሳብ አፍላቂዎችና መሪዎች ጋር ተገናኙ | የአፍሪካ የወደፊት የፖለቲካ፣ የንግድ፣ የምህበራዊ ተቋማት መሪ የሆኑ ወጣቶች እርስ በርስ ልምድ ይለዋወጣሉ፤ ከታላላቆቻቸውም ተሞክሮ ይካፈላሉ። | ጉባኤው እስከ ሀሙስ ድረስ ይቀጥላል ከ45 የአፍሪካ አገሮች የተሰባሰቡት 115 ወጣቶች ዛሬ ማለዳ በውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ለአራት ቀናት የሚዘልቀውን ውይይታቸውንና የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብራቸውን ጀምረዋል። እነዚህ በሚኖሩበት አገር በአነስተኛና ከፍተኛ የማህበራዊ መሪነት ጉልህ ሚና የተጫወቱ ወጣቶች ለአፍሪካ የወደፊት ተስፋዎቿ፣ አሁን ደግሞ የእድገት ክንዶቿ ናቸው ሲሉ የዩናይትድ ስቴይትስ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆኒ ካርሰን በስብሰባው መክፈቻ ተናግረዋል። በርካታ የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ-ግዛት ነጻ... |
a_amh-wfp-famin-7-21-11-125957683_1459934 | https://amharic.voanews.com/a/amh-wfp-famin-7-21-11-125957683/1459934.html | በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ከብቶች እየሞቱ ነው | በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ፣ በሶማሊያና በኬንያ የተከሰተው ድርቅ ወደርሃብ በመሸጋገር ላይ በመሆኑ ከፍተኛ እልቂት ሊያስከትል ይችላል ሲሉ የዓለም የምግብ ድርጅትና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አስጠነቀቁ። | በሶማሊያ የተከሰተው ድርቅ ወደርሃብ መሸጋገሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ እርዳታ በማይደርስባቸው የሶማሊያ ደቡባዊ ቀጣናዎች ድርቅ ያስከተለው ከፍተኛ የምግብ ዕጥረት ዕለቂት ሊያስከትል ወደሚችል ርሃብ መሽጋገሩን የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ይፋ አደረጉ። የአፍሪካ ህብረትና የዓለሙ ድርጅት የደረሰውን ሰባዊ ቀውስ ለመታደግ በትብብር እንዲንቀሳቀሱ ጠየቁ። የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጆሴት ሽራም ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ኢራስተስ ሞኤንቻ ጋር በመሆን በ... |
a_voa-radio-mag-stories-with-alula-kebede-and-addisu-abebe-11-22-15_3073955 | https://amharic.voanews.com/a/voa-radio-mag-stories-with-alula-kebede-and-addisu-abebe-11-22-15/3073955.html | የሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች፥ አዲሱ ሰባት ኪሎ መጽሔት፥ እና ሌሎች ሙዚቃ ነክ ወጎችና የሃሳብ መስመሮች፤ | የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ። | “ሰባት ኪሎ” የሚል ሥያሜ ስለ ሰጡትና በቅርቡ ለንባብ ስለ በቃው መጽሔታቸው፥ ጋዜጠኝነት በስደትና መንገዶቹ የሚያወጉን እንግዶች፤ ከቀድሞዎቹ አዲስ-ነገሮች ሁለቱ ለራዲዮ መጽሔት ወግ ተሰይመዋል። ከዓመታት በፊት “መርካቶ ሰፈሬ፤” በተሰኘችው ዜማው ከሙዚቃ አድናቂዎች ጋር የተዋወቀው ድምጻዊ አብዱ ኪያር “ጥቁር አንበሳ” በሚል ሥም ያወጣውን አዲስ አልበም ይዞ ብቅ ብሏል። በእንግሊዥናው ምሕጻረ ቃል AFRIMA በመባል ለሚታወቀው “የመላው አፍሪቃ ዓመታዊ የሙዚቃ ሽልማት” ለሁለተኛ ጋዜ ከተመረጠችው ድምጻዊ... |
a_a-53-2008-04-30-voa2-93031129_1457722 | https://amharic.voanews.com/a/a-53-2008-04-30-voa2-93031129/1457722.html | African Athletics Championships DAY 1: Ethiopia Sweeps Medals in the Men’s 10,000 meters | Gebreegziabher Gebremariam led the Ethiopian trio to victory and finishing the10,000 meteres in 28:17.11. | 10,000 m - MENS FINAL RANK NAME NAT 1. Gebregziabh. GEBREMARIAM ETH 28:17.11 2. Ebrahim JEILAN ETH 28:30.66 3. Eshetu WONDEMU ETH 28:56.36 4. John KORIR KEN 29:07.33 5. Bernard SANG KEN 29:47.61 6. Julius KIPTOO KEN 30:12.10 SHOTPUT - MENS FINAL RANK NAME NAT RESULT 1. Abdu Moaty MOUSTAFA EGY 18.06 2. Yasser IBRAHIM EG... |
a_inventions-for-though-times-3d-printers-ppe-faruk-mubarek-with-voa-alula-kebede-may-2020_5437346 | https://amharic.voanews.com/a/inventions-for-though-times-3d-printers-ppe-faruk-mubarek-with-voa-alula-kebede-may-2020/5437346.html | ሕይወት ለማዳን የዋለ ጥበብ እና አሳቢነት | “እንደሚታወቀው አገራችን ደካማ የሚባል የጤና ሥርዓት ነው ያላት አገር ነች። ከዚህ በፊት በተክለምዶ የተለያዩ እርዳታዎች ከውጭ ይመጡ ነበር። አሁን ግን ያደጉትን አገሮች ብንመለከት አራቸውን ዘግተው ራሳቸውን ለማዳን እየተረባረቡ ናቸው። ‘የስሪ ዲ ኮሚኒቲዎች’ እና ቴክኖጂውንም ሳይ ደግሞ ብዙው የውሚሰሩት ራሳቸውን ለመጥቀም ነው። ስለዚህ እኛም ለምን ይሄንን ወስደን ራሳችንን ለምን አናድንም ከሚል ነው የተነሳሁት።” ፋሩቅ ሙባረክ። | ዋሽንግተን ዲሲ - አዲስ አበባ — ክፍል ሁለት ከጊዜያችን ብርቱ ፈተናዎች አንዱ ለሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ የሚውሉ ሁነኛ መላ ፍለጋ የሚደረገው ጥረት በሁሉም አቅጣጫ ቀጥሏል። በዚህ መላውን የሰው ልጆች በገጠመ ፈተና እንደየተሰማሩበት ሞያና እንደየክህሎቶቻቸው የተያዘው ጥረት አጋዥ ለመሆን የበኩላቸውን ለማድረግ ደፋ ቀና የሚሉት ብዙዎች ናቸው። የወረርሽኙን የጥድፊያ መዛመት ለመግታትት ሁነኛ የመከላከያ ብልሃቶችን በመቀየስ አገራዊውን ጥረት ከሚያጎለብቱት፤ ከፍተኛ እጥረት የሚታይባቸውን አስፈላ... |
a_south-sudan-independence-7-11-2011-125348308_1459557 | https://amharic.voanews.com/a/south-sudan-independence-7-11-2011-125348308/1459557.html | የደቡብ ሱዳን አስተዳድር ከጎረቤቶቹ ጋር አብሮ ለመስራት እጁን ዘረጋ | ሀምሌ 2 ቀን 2003ዓም የአለማችን አዲሲቱ አገር ደቡብ ሱዳን ተወለደችበት እለት ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ባሰሙት ንግግር አገራቸው የመልካም ጉርብትናና የትብብር እጇን እንደምትዘረጋ ገልጸዋል። | ቅዳሜለት በመዲናዋ ጁባ በተደረገ ስነስርዓት በአስር ሽዎች የተቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ዜጎች በአለም መሪዎች ታዛቢነት የአዲስ አገር ምስረታ በዓላቸውን አክብረዋል። ከዋዜማው ጀምሮ ማምሻውን በጸሎትና በባህላዊ ጭፈራዎች ደምቆ ያመሸው የነጻነት ዋዜማ፤ ቅዳሜ ማለዳ ባንዲራ ይዘው ለነጻነት ክብረበዓሉ በወጡ ዜጎች ታጅቦ፣ በአለም መሪዎች ታዛቢነት ተበስሯል። የደቡብ ሱዳን አስተዳድር ፕሬዝደንት የነበሩት ሳልቫ ኪር፤ የአዲሱቱ አገር ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ ማሃላ ፈጽመዋል፤ ሃገሪቱ የምትተዳደርበትን ህገ-መን... |
a_usaid-officials-ethiopia-127886433_1462105 | https://amharic.voanews.com/a/usaid-officials-ethiopia-127886433/1462105.html | የ United States አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት አሞገሱ | የ United States የአለም አቀፍ ረዴት ባለስልጣን በኢትዮጵያ ረሀብ እንዳልጋባ ገለጹ | የ United States አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ገለጹ። አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎችም እርዳታውን እያገኙ ናቸው ብለዋል ባለስልጣናቱ። በ United States አለም አቀፍ የተራዶ ድርጀት ከፍተኛ ምክትል የእርዳታ አስተባባሪ Gregory Gotlied በአዲስ አበባ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ሲም አልሱ፣ “በኢትዮጵያ ረሃብ የለም እንላለን። አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በሱማልያ ያለውን ሁኔታ ... |
a_meles-press-conference-05-27-10-95042384_1462514 | https://amharic.voanews.com/a/meles-press-conference-05-27-10-95042384/1462514.html | ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎችን ነቀፉ፤ | "የምርጫው ውጤት ትብብራችንን ለመቀጠል የሚያስችል አይደለም ብለው የሚያስቡ ከሆነ - መልካም፤ እስከዛሬ ላደረጉልን እርዳታ እያመሠገንን ወደፊት መቀጠል ነው፡፡" መለስ ስለዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አቋም ሲናገሩ፡፡ | መለስ ዜናዊ “የአውሮፓ ኅብረት ታዛቢዎች የፖለቲካ ድምዳሜውን ለራሣቸው ዓላማ በሚመጥን መልኩ የሰፉት ስለሆነ እኛ ልንለብሰው አንችልም’ አሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ትላንት በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርተዋል፡፡ የሃገር ውስጥና የውጭ ጋዜጠኞች ያነሷቸው ጥያቄዎች ከምርጫው ጋር የተያያዙ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ጥያቄዎች መካከል አንዱ ካለፉት ምርጫዎች ሁሉ በተለየ ሁኔታ ገዥው ፓርቲ ከሁለት መቀመጫዎች በስተቀር የፓርላማውን መቀመጫዎች ጠቅልሎ መውሰዱ "በሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደትና በብ... |
a_amh-onlf-sweeds-ethiopia-7-5-11-125030254_1463114 | https://amharic.voanews.com/a/amh-onlf-sweeds-ethiopia-7-5-11-125030254/1463114.html | ሁለት ስዊድናዊ ጋዜጠኞች በኦጋዴን በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ቆስለው ታሰሩ | በሰሜናዊቷ የሶማሊያ ራስ ገዝ ፑንትላንድ በኩል ድንበር ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ያቀኑት ስዊድናዊ የፎቶ ጋዜጠኞች በኦብነግ አማጺያን አጃቢነት ድንበር ሲሻገሩ በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ቆስለው ታስረዋል። | ሰኔ 23 ቀን ኢትዮጵያን በሚያዋስነው የፑንትላንድ ድንበር በጋልቃዮ በኩል ሁለቱ ስዊድናዊ ጋዜጠኞች ከከኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጭ ግንባር (ኦብነግ) ታጣቂዎችና ሌሎች አጋዦቻቸው ጋር ሲጓዙ ነበር የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በደረሳቸው መረጃ መሰረት ተከታትለው ያገኟቸው። ወዲያውኑ ተኩስ ተከፈተ። የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ በረከት ስምዖን የሆነውን ለVOA እንዲህ ያስረዳሉ። “ተኩስ ነበር። በዚህ የተኩስ ልውውጥ 15 የአሸባሪ ድርጅቱ ታጣቂዎች ወዲያውኑ ተገድለዋል። ስድስቱ ተማርከዋል። ከዚህ በተጨ... |
a_ethiopia-edp-election-95273224_1458296 | https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-edp-election-95273224/1458296.html | የ2002ቱ አጠቃላይ ምርጫ ነፃና ፍትሃዊ አልነበረም፤ በበርካታ ችግሮች የተሞላም ነበር፤ ሲል ኢዴፓ አስታወቀ | ምርጫው ተመልሶ ቢደገምም፤ በዴሞክራሲ ተቋማቱ የሚታዩ ግድፈቶች በድጋሜ ለገዥው ፓርቲ ያዳላሉ ሲሉ የኢዴፓ አመራሮች አስታውቀዋል። | ከህግ ውጭ ከአንድ በላይ የኢህአዴግ ወኪል ታዛቢ በየምርጫ ጣቢያዎች ተመድቦ እንደነበር ይላል ኢዴፓ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ 547 መቀመጮች ካሉት የአገሪቱ ፓርላማ ከ99.6 በመቶ በላይ የሚሆነውን ማሸነፉ ከተነገረ በኋላ ተቃዋሚዎች ውጤቱን አስመልክቶ ያላቸውን አስተያየት በመግለጫዎች ጭምር እያስታወቁ ነው። በሸንጎው ወንበሮች ባያሸንፉም የተሻለ ድምፅ ማግኘታቸው ከተነገረላቸው ሁለት ዋነኛ ተቃቃሚዎች አንዱ የሆነው ኢዴፓም በዛሬው ዕለት በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ አቋሙን ይፋ አድርጓል። የፓርቲው ሊቀ መንበር አ... |
Dataset Card for LR-Sum
LR-Sum is a automatic summarization dataset of newswire text with a focus on less resourced languages with a cc-by 4.0 license.
Dataset Details
Dataset Description
LR-Sum is a permissively-licensed dataset created with the goal of enabling further research in automatic summarization for less-resourced languages. LR-Sum contains human-written summaries for 39 languages, many of which are less-resourced. The data is based on the collection of the Multilingual Open Text corpus where the source data is public domain newswire collected from from Voice of America websites. LR-Sum is released under a Creative Commons license (CC BY 4.0), making it one of the most openly-licensed multilingual summarization datasets.
- Curated by: BLT Lab: Chester Palen-Michel and Constantine Lignos
- Shared by: Chester Palen-Michel
- Language(s) (NLP): Albanian, Amharic, Armenian, Azerbaijani, Bengali, Bosnian, Burmese, Chinese, English, French, Georgian, Greek, Haitian Creole, Hausa, Indonesian, Khmer, Kinyarwanda, Korean, Kurdish, Lao, Macedonian, Northern Ndebele, Pashto, Persian, Portuguese, Russian, Serbian, Shona, Somali, Spanish, Swahili, Thai, Tibetan, Tigrinya, Turkish, Ukrainian, Urdu, Uzbek, Vietnamese
- License: CC-BY 4.0
Dataset Sources [optional]
Multilingual Open Text v1.6 which is a collection of newswire text from Voice of America (VOA).
- Paper: https://aclanthology.org/2023.findings-acl.427/
- Repository: https://github.com/bltlab/lr-sum
Uses
The dataset is intended for research in automatic summarization in various languages, especially for less resourced languages.
Direct Use
The data can be used for training text generation models to generate short summaries of news articles in many languages. Automatic evaluation of automatic summarization is another use case, though we encourage also conducting human evaluation of any model trained for summarization.
Out-of-Scope Use
This dataset only includes newswire text, so models trained on the data may not be effective for out of domain summarization.
Dataset Structure
Each field is a string:
{
'id': Article unique id
'url': URL for the news article
'title': The title of the news article
'summary': The summary of the article
'text': The full text of the news article not including title
}
Dataset Creation
Curation Rationale
Research in automatic summarization for less resourced languages.
Source Data
Voice of America (VOA)
Data Collection and Processing
See our paper for details on collection and processing.
Who are the source data producers?
Voice of America (VOA)
Annotation process
The summaries are found in news article meta data. More detail about the curation process can be found in our paper.
Who are the annotators?
The summaries are found in the news article meta data. The authors of the summaries are authors and staff for VOA.
Personal and Sensitive Information
The only sensative personal information would be information already published in news articles on VOA. See VOA's mission and values
Bias, Risks, and Limitations
The content in this dataset is newswire. See VOA's mission and values for more detail about the journalistic integrity and policy.
Recommendations
The data is newswire text. Training text generation models on this dataset will have similar risks and limitations to other text generation models including hallucinations and potentially inaccurate statements. For some languages that have fewer examples, issues with text generation models are likely to be more pronounced. The dataset is primarily released for research despite having a permissive license. We encourage users to thoroughly test and evaluate any models trained using this data before putting them into production environments.
Citation
If you make use of this dataset, please cite our paper using this bibtex:
BibTeX:
@inproceedings{palen-michel-lignos-2023-lr,
title = "{LR}-Sum: Summarization for Less-Resourced Languages",
author = "Palen-Michel, Chester and
Lignos, Constantine",
editor = "Rogers, Anna and
Boyd-Graber, Jordan and
Okazaki, Naoaki",
booktitle = "Findings of the Association for Computational Linguistics: ACL 2023",
month = jul,
year = "2023",
address = "Toronto, Canada",
publisher = "Association for Computational Linguistics",
url = "https://aclanthology.org/2023.findings-acl.427",
doi = "10.18653/v1/2023.findings-acl.427",
pages = "6829--6844",
abstract = "We introduce LR-Sum, a new permissively-licensed dataset created with the goal of enabling further research in automatic summarization for less-resourced languages.LR-Sum contains human-written summaries for 40 languages, many of which are less-resourced. We describe our process for extracting and filtering the dataset from the Multilingual Open Text corpus (Palen-Michel et al., 2022).The source data is public domain newswire collected from from Voice of America websites, and LR-Sum is released under a Creative Commons license (CC BY 4.0), making it one of the most openly-licensed multilingual summarization datasets. We describe abstractive and extractive summarization experiments to establish baselines and discuss the limitations of this dataset.",
}
Dataset Card Authors
Chester Palen-Michel @cpalenmichel
Dataset Card Contact
Chester Palen-Michel @cpalenmichel
- Downloads last month
- 1,224